በጉ/ክ/ከ/ወ/4/ፋ/ጽ/ቤት/ በ2019 የበጀት ዓመት ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያወች፣ሎት 2 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ሎት 4 የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት፣ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት፣ሎት 7 የህትመት ውጤቶች፣ሎት 8 መስተንግዶዎችን፣ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፤ሎት 10 የዲኮር ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/4/ፋ/ኢ/ጽ/ቤት/001/2019
በጉ/ክ/ከ/ወ/4/ፋ/ጽ/ቤት/ በ2019 የበጀት ዓመት ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያወች፣ሎት 2 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ሎት 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ሎት 4 የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ሎት 5 የደንብ ልብስ ስፌት፣ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት፣ሎት 7 የህትመት ውጤቶች፣ሎት 8 መስተንግዶዎችን፣ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና፤ሎት 10 የዲኮር ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ
1. ከሚዛው ዕቃ /አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር Tin No ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ5ዐሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ የሎት 1 30,000.00 ብር፣ ሎት 2- 30,000.00 ብር፣ ሎት 3 ብር 2,500.00፣ ሎት 4- ብር 25,000.00፣ ሎት 5 ብር 5,000.00፣ ሎት-6 ብር 1,500.00፣ ሎት 7 ብር 2,000.00፣ ሎት 8 ብር 2,000.00 ፤ ሎት-9 ብር 2,000.00፤ ሎት10- ብር 1500 በወረዳ 4 ፋይናንስ ስም በተዘጋጀ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
5. ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በፖስታ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ እና በተጨማሪም ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነድ የሚል ፅሁፍ በሰነዱ ላይ መገለፅ እንዲሁም የአቅራቢ ድርጅት ማህተም ሊሰፍርበት ይገባል። ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣ ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት በተመረጠው ሳምፕል ጥራት መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታው ሣጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎች፤ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆች፤ የተለያዩ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፤ የህትመት ውጤቶች፤ የዲኮር ስራዎች መስተንግዶዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ጥራት ለመለየት የሚያስችልና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01በሚገኘውግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ወረዳ4 እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፣
11. የጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች እሴት ባልጨመሩባቸው ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነድ እንደማንኛውም ነጋዴ ገዝተው የሚወዳደሩ መሆኑንመ/ቤቱ ያሳውቃል።
12. መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ከውል በፊት 20%/ሀያ ከመቶ/ጨምሮ ወይም20% ቀንሶ እና 25% ጨምሮመግዛት ይችላል፣
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው የተሸለ መንገድ ካገኘ በጨታዉ አይገደድም።
14. ሎት 6፤ ትንስፖርት አገልግሎት ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተወዳዳሪ የሆናችሁ ወይም ቲኦቲ/2%/ ተመዝጋቢዎችን የሚያካትት መሆኑን እናሳዉቃለን
አድራሻ፡- ናይጀሪያ ኤምባሲ ወደቀጨኔ መድኃኒዓለም በሚወስደው መንገድ ላይ ጉ/ክ/ከ/ወ/4/አስ/ፋ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ ወይም
በስልክ ቁጥር 011 126 6936 መደወል ይችላሉ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
