Tender Detail

Tender Details


በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ሜዲካል አክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ (4500 ሰዓት) የቡስተር (RIX booster and AirSep oxygen generator) እንዲሁም ኤር ኮምፕረሰር (kaeser compressor) ለጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን ግዥ ማዕከሉ በሚያቀርበው መሰረት በማሟላት አጠቃላይ ጥገና ማድረግ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ ጤና ቢሮ የአማራ ሜዲካል አክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል 2018 በጀት ዓመት ክስጅን ማምረቻ ማዕከሉ (4500 ሰዓት) የቡስተር (RIX booster and AirSep oxygen generator) እንዲሁም ኤር ኮምፕሪሰር (kaeser compressor) ለጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን ግዥ ማዕከሉ በሚያቀርበው መሰረት በማሟላት አጠቃላይ ጥገና ማድረግ ይፈልል፡፡ በመሆኑም በደሴ ቅርንጫፍ እና በባህር ዳር የሚገኙ ማሽኖች መለዋወጫዎችን ግዥ ስለሚያስፈልጋቸው

በዘርፉ የተሰማራችሁ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሞሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያላቸው
  3. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ / ብር በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች 1ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ውድድሩ በሙሉ ሰርቪስ ማድረግ ስለሆነ ከፋፍሉ መሙላት አይቻልም፡፡ ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሙላት አለባቸው
  6. ስለ ጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ /ስፔክ/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከፍሎ በመውሰድ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ስራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 3% (ሶስት ፐርሰንት) በባን የተረጋገጠ ፍያ ትዕዛዝ (..) ዌም በማዕከሉ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በዋጋ ማቅረቢያው ቅጽ መሰረት የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በመሙላትና በየገጹ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተማ ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከሉ የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ለዚሁ ተብሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት 1130 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሳጥኑም በዚሁ ዕለት 1130 ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ይከፈታል፡፡ በዓል ወይም ምዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ማእከሉ ጨረታውን የመፈት መብት አለው፡፡
  11. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በመሉ ወይም በከፊል የማረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0583200415/0583201992 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0593203088 መጠየቅና ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ- ህይወት አጠቃ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ጎን

ባህርዳር

 

የአማራ ሜዲካል ኦክስጅ ምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል

 

Save Tender