Tender Detail

Tender Details

  • Company Geda Transport and Logistics S.C. (ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ አ.ማ)
  • Address ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮልጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 558 25 19
  • Websitehttps://www.gedatransport.com/#
  • Deadline29 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-09-29 00:00:00
  • Categories Vehicle

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡


                                                           የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር [Gada/NCB/03/2018] 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ የተለያዩ ያገለገሉ የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 

  1. ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና የታደሰ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ወይም ያላት እና በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ወይም የተሰማራች፡፡ 

  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡ 

  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም ወይም በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 

  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበትን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ሁሉንም ሰነዶች ደግሞ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

  5.  የጨረታ ሰነድ የገዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ ተሽከርካሪዎችን ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል 

  6. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ 

  7. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡ 

  8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

  9. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 አድራሻ:- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ስበስጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር:- 011-558-25-19/0991330694/0909273110

                                                                        ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አ.ማ

Save Tender