ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ዉብሸት ጥላሁን ሀይሌ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዡ የተዘረዘውን መኪና በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ዉብሸት ጥላሁን ሀይሌ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን በሰንጠረዡ የተዘረዘውን መኪና በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሸሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመኪናውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማሲያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ ፣ የድርጅቱ መመስረቻ ጹሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ፀድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የአሲያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራጮች ያሲያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፤ ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላሉ።
- ተጫራጮች መኪናዉን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- የጨረታው የሚካሄደው ፀደይ ባንክ ዋናዉ መስሪያቤት 9ኛ ፎቅ ነው።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939115010 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም
|
የመያዣ ስጪ ስም |
የተሽከርካሪው አይነት |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የጨረታ ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የወጣው |
|
|
1 |
አቶ ውብሸት ጥላሁን
|
አቶ ውብሸት ጥላሁን |
የ2022 ስሪት CZF63S ሞዴ፤ በቤንዚን የሚሰራ፤ 4 ሰው የመጫን አቅም ያለው፤ 1200 ሲሲ፤ ባለ 4 ሲሊንደር እና 82 የሞተር ፈረስ ጉልበት ያለው፤ ጃፓን ሱዚኪ ዲዛየር አውቶሞቢል |
K12MP435 1306 |
MBHCZF6 3S00337105 |
2,363,961.60 (ሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አንድ ብር ከ 60 ሳንቲም) |
መስከረም 27/2017 ዓ/ም |
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት-6፡00 ሰዓት |
ለሁለተኛ ጊዜ |
