Tender Detail

Tender Details


በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ1ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎችን፤ ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎችን በሎት 3 የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እንዲሁም በሎት 4 የተለያዩ የግንባታና የቧንቧ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት 2018 በጀት 1 ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የጽሕፈት ዕቃዎችን፤ ሎት 2 የተለያዩ ዳት ዕቃዎችን በሎት 3 የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እንዲሁም በሎት 4 የተለያዩ የግንባታና የቧንቧ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው

  1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፡
  2. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
  5. የዘመኑ ግብር የከፈለ/ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን/በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ሕጋዊ የውልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፉ ድምር ከተሠራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የእንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው ሳምፕላቸው በማ//ቤቱ ለሚቀርቡ እቃዎች እና ሳምፕል የሌላቸው ዕቃዎች በእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል፤ ሳምፕላቸው በተጫራቾች ለሚቀርቡ እቃዎች ጥራት ያለው ዕቃ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል፡፡
  11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደሩበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  13. ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. የጨረታ አሸናፈዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም ፍያ ዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ /ቤቱ ፋይናንስ ዴስ በሥራ ቀንና ሰዓት 13/01/2018 / ጀምሮ እስከ 21/01/2018 . ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን 22/1/2018 . ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 700 ሰዓት ድረስ በማ//ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። 23/1/2018 . ተጫራቾች ወይም /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማ//ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 8:30 ላይ ጨረታው ይከፈታል በተጫራቾች የሚቀርቡ ሳምፕሎች የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ላይ ከዋሉበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ እስከሚጠናቀቅበት ቀን ድረስ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች //ቤቱ በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ//ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን ረጋግጦ ማስረከብ አለበት፡፡ የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ሕጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሬጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  19. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት //ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው
  21. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ሕጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በሥራ ሰዓት ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

 

የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና //ቤት

 

Save Tender