Tender Detail

Tender Details

  • Company Federal Housing Corporation (የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን)
  • Address ዋና መ/ቤት የድሮ መርከብ ሕንፃ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አጠገብ ያለው ሕንፃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115539535
  • Websitehttps://www.fhc.gov.et/en#New
  • Deadline09 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-10-09 00:00:00
  • Categories Building Materials

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል እና ለተለያዩ ፕሮጄከቶች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ማለትም በሎት ዐ1 የተመደቡ ጠጠር (00፣ 01 እና 02) እና በሎት oz የተመደቡ የመንዝ አሸዋ ቀይ አሸዋ (ሬድኣሽ) እና ኮሚቼ (ፑሚስ) ገላን ለሚገኘው የማምረቻ ማዕከል ድረስ ከሚያቀርብለት አምራቾች ወይም አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ./ዕ.ግ/29/1/2018 ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ መስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕ.ግ/29/2018

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል እና ለተለያዩ ፕሮጄከቶች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ማለትም በሎት ዐ1 የተመደቡ ጠጠር (00፣ 01 እና 02) እና በሎት 02 የተመደቡ የመንዝ አሸዋ ቀይ አሸዋ (ሬድኣሽ) እና ኮሚቼ (ፑሚስ) ገላን ለሚገኘው የማምረቻ ማዕከል ድረስ ከሚያቀርብለት አምራቾች ወይም አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ./ዕ.ግ/29/1/2018 ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ግብዓቶች ግዥ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ትራንስፖርትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ በተለያዩ ፖስታ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልከቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊከ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በዘርፉ የስራ ልምድ ያላቸው እንዲሁም የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።

4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሃር በሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ) ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡ 15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች ግብዓቶቹን የማምረቻ ማዕከል ግቢ ድረስ ያቀርባሉ።

7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስልክ ቁጥር 011-855-30-35/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

Save Tender