የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በግቢ ውስጥ ለሚሰሩ የግንባታ እና የጥገና ስራዎችን በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-የማ/ብ/002/2018
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በግቢ ውስጥ ለሚሰሩ የግንባታ እና የጥገና ስራዎችን በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሸነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የስራ ቦታ |
ወረዳ |
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
የተቋራጭ ደረጃ |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
|
1 |
የማነብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ለሚሰራው የግንባታ እና ጥገና ስራዎች |
06 |
50,000.00 |
ደረጃ GC7/BC 6 እና ከዚያ በላይ የሆነ ተቋራጭ |
90 ቀን |
ለሥራው የንግድ ምዝገባ እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ 2017ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ከፌዴራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ከገቢዎች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list)፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።
ተጫራቾች የጨረታ ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ፊርማ ማህተም እና የሚወዳደበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND OR BID SECURIY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመፃፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግንባታውን ዓይነት፣ ዝርዝር መግለጫ፣ ስራ ዝርዝር፣ መመሪያ/ሰነድ ከመ/ቤታችን ግዥ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ
ማሳሰቢያ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
ተጫራቾች ለ90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND OR SECURITY) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (UN-CONDITIONAL BANK GUARANTEE) በኮ/ቀ/ክ/ከ/የማነብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለበት።
ተጫራቾች በጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቾቹ የዋጋ ትንታኔ (COST BREAK DOWN) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ (UN-BALANCED RATE) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል።
ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned rate correction) እና ነጠላ ዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for rate correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነፃ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያ በሚያዘው መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ከሚሰራው ስራ ጋር ተመሳሳይነት ይዘት ያለው እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ከመንግስት ተቋማት ማቅረብ የሚችሉ።
ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር አደባባይ ገባ ብሎ የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ስልክ፡- 011-3-69-68-14 / 011-3-49-09-98
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
