የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳር ብዛት 25
- በፀሐይ ሃይል የሚሰሩ የትራፊክ አደጋ ማስጠንቀቂያ መብራት (Solar Powered traffic warning light) ብዛት 94
- የትራፊክ ማስተናበሪያ ዱላ (traffic Stick light) ብዛት 81
- የትንፋሽ አልኮል መጠን መለኪያ (Alcohol tester) ብዛት 45
- ሞንታርቦ
- ሚክሰር
- አምፕሊፋር
- ሆርን
የገዥ መለያ ቁጥር : መ.ደ.መ.ፈ.አ 001/2018
የገዥ ዓይነት፡ ግልጽ ጨረታ
ጨረታው የሚወጣበት ቀን መስከረም 2018 ዓ.ም
ተጫራቾች ትክክለኛ አቅራቢ ስለመሆናቸው ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት እና የጨረታ መሳተፈያ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና ላሸነፉበት ዕቃ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራ ቦታ ወይም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የስራ ቦታቸውን ለማሳየት ፈቃደኛ የሆኑ፣
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በተቋሙ ስም የተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000983997 ላይ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል በመቅረብ የጨረታውን ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለጹት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በተመሳሳይ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉም ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚወዳደሩበትን በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍ እና የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ እና ድምር ዋጋ ቫት ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ስፔስፊኬሽን መሰረት ወይም በሚቀርበው ናሙና ጥራት ዋስትና አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረቢያ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል። የሚወዳደሩበትን ዕቃ በፖስታ አሽጎ በፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ እና የድርጅቱ ስም መጻፍ እና ማህተም ማድረግ ግዴታ ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ በወጣው ስፔስፊኬሽን /መስፈርት/ መሰረት የማቅረብ ግዴታ ይኖረዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ ቢያንስ የአንድ ዋስትና መስጠት አለባቸው።
- ተጫራቹ ያሸነፈበት ዕቃ /ዕቃዎች/ በሙሉ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የሚቀርቡ ዕቃዎች በተቋሙ የበላይ ኃላፊ ኃላፊነቱ የሰጠው አካል ስለ ዕቃው ትክክለኛነት ሲረጋገጥና አቅራቢ ሕጋዊ ደረሰኝ ሲያቀርብ ክፍያው ይፈፀማል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የጠበቀ ነው፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው፡፡
- ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በኤንቨሎፕ በተናጠል /ለየብቻ/ ማህተም ያረፈበት በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከዚህ በላይ የጠቀሱትን መስፈርት የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡
- በጨረታው ሳጥን መክፈቻ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ከተቋሙ እውቅና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ካሳንቺስ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዲሱ ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ የስራ ክፍል
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር፡- 09-11 54 83 75 ወይም 09-21 56 22 62
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት
