ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ትርፋማ ያልሆነ በሲቪል ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. 2004 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ ያለ የውጭ ድርጅት ነው። በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ አዲስ በተከራየው ህንፃ ላይ የተለያዩ ቢሮዎችን በአሉሚኒየም እና ጂፕሰም አከፋፍሎ ለመስራት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተቋራጮች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ለቢሮ ክፍልፋይ ግንባታ ስራ
(Office Partition Works)
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ትርፋማ ያልሆነ በሲቪል ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. 2004 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ ያለ የውጭ ድርጅት ነው። በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ አዲስ በተከራየው ህንፃ ላይ የተለያዩ ቢሮዎችን በአሉሚኒየም እና ጂፕሰም አከፋፍሎ ለመስራት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተቋራጮች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም በሥራው ብቃትና ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ተቋራጮች ቢሮ በአካል በመቅረብ የስራ መዘርዝር በመውሰድ መወዳድር ትችላላችሁ።
ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ
- የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ማንኛዉም ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመቅረብ የዋጋ ዝርዝር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታው መዝጊያ ቀን በ9:00 ሰዓት ይከፈታል። ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ጽ/ቤት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ቤት ቁጥር 765/04 አዲስ አበባ፣ ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍ ብሎ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 267151/267950. +251913258163 መደወል ይችላሉ።
