Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Center for Development /ECD/ /ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት/
  • Address ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0982-882826
  • Websitehttps://ecdethiopia.org/
  • Deadline03 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2025-10-03 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በፕሮጀክቱ በአጋር ትምህርት ቤቶች ላይ የተሰሩ ሥራዎችን በቪዲዮ እና በህትመት መልክ በመሰነድ ለልምድ ልውውጥ እና ለመማሪያ እንዲሁም ወደፊት ለሚቀርጹ ለሌሎች ፕሮጀክቶች እንደ ግብዓት እንዲያገለግል ለማድረግ ታቅዷል። በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።


 

የቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና የመጽሔት ህትመት

ጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስድስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህናፃት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅት ጋር በመሆን Mobile Toolkit for Climate Resilience የሚል ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በፕሮጀክቱ በአጋር ትምህርት ቤቶች ላይ የተሰሩ ሥራዎችን በቪዲዮ እና በህትመት መልክ በመሰነድ ለልምድ ልውውጥ እና ለመማሪያ እንዲሁም ወደፊት ለሚቀርጹ ለሌሎች ፕሮጀክቶች እንደ ግብዓት እንዲያገለግል ለማድረግ ታቅዷል።

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. በቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና ህትመት ሥራ ልምድ ያላቸው፣ እንዲሁም
  5. ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ሥራዎች መሥራታቸውን የሚያሳይ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት እለት አንስቶ 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ በነጻ በመውሰድ የቪዲዮ ፕሮዳክሽኑን እና ህትመቱን የምትሰሩበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ አድርጋችሁ እንድትወዳደሩ እንገልፃለን።

አድራሻ፡ -ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዲቨሎፕመንት /ECD/

ቦሌ አለም ህንፃ 7 ፎቅ

ስልክ፡- 0982 882 826

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ በትክክል ካልተገለጸ ዋጋው ቫት እንደተካተተ ተደረጎ ይቆጠራል።
  2. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት

 

Save Tender