የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ግቢ የሠራተኞች ካፌ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ግቢ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሰረት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፤
ሎት-1 የሠራተኞች ካፌ
- ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
- ሙሉ የካፍቴሪያ ዕቃዎችን በራሱ አሟልቶ መሥራት የሚችል።
- ካፌውን በራሱ ወጪ አድሶ መሥራት የሚችል።
- የካፍቴሪያ አገልግሎት ለኮሌጁ ሠራተኞች እና ሠልጣኞች በተመጣጣኝ ዋጋ እና ጥራት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
- ስርዝ ድልዝ ሳይኖርው ግልጽ እና ዋጋው በሚታይ መልኩ በመሙላት የኮሌጁ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት አለባችሁ።
- ከስድስት ወር በፊት ምንም አይነት ዋጋ መጨመር አይቻልም።
- የውል ማስከበሪያ ጋራንቲ ማቅረብ አለበት።
ማሳሰቢያ፡- ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ 4፡30 በኮሌጁ ላይብረሪ በጨረታ ቡድኑ የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከሶስት መቶ በላይ ለኮሌጁ ሠራተኞች አገልግሎት መሰጠት የሚችል።
አድራሻ- ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋናው ግቢ በመሰረት ሕንፃ ገባ ብሎ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4
ስልክ ቁጥር፡- 011-470-41:
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
