በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን የግብርና ምህንድስና ቴክኖሎጂዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የብዜት ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግ.ጨ 02/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን የግብርና ምህንድስና ቴክኖሎጂዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የብዜት ሥራውን ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- 1ኛ በሞተር የሚሰራ የማሽላ መውቂያ ብዛት 2 (ሁለት)
- 2ኛ የእርድ መቆራረጫ ቴክኖሎጂ ብዛት 6 (ስድስት)
- 3ኛ የመኖ መከረታተፍያ ብዛት 4 (አራት)
- 4ኛ የካዛቫ መቆራረጫ ቴክኖሎጂ ብዛት 4 (አራት)
- 5ኛ በሞተር የሚሰራ ሁለገብ መውቂያ ከኢንጂን ጋር (Cleaning type) ብዛት 2 (ሁለት)
ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ከዚህ በፊት በሥራ ሂደታችን ወይም በተመሳሳይ የግብርና ሜካናይዜሽን ምርምር ማዕከላት ለእነዚሁ ከላይ ለተዘረዘሩት ቴክኖሎጂዎች ለማባዛት ሥልጠና ወስደው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተቀባይነት ያለው የማምረቻ ጥሬ ዕቃን የገበያ ዋጋን ያገናዘበ፣ ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን ለከፍተኛ ወጪ የማይዳርግ ማስተማመኛ በመስጠት የብዜትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆኑና ከዚህ በፊት በመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል በሜካናይዜሽን ስምምነት ወስደው ያመረቱና ልምድ ያላቸው (Success story) እንደ መረጃ ማያያዝ የሚችሉና ከላይ በቀረቡት ዝርዝር መግለጫ መሰረት የብዜት ቴክኖሎጂዎችን አምርተው የሚያውቁና የማምረቻ ወሳኝ የሚባሉ ማሽኖች ያላቸውና በአካል የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማባዛትና በቅድሚያ የሚባዙ ቴክኖሎጂዎችን ማዕከሉ ድረስ በመምጣትና በማየት መወዳደር የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ16 (አስራ ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረ ቼክ CPO በማስያዝ ከአዳማ ወደ አሰላ በሚወስደው መንገድ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ ከገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 800 (ስምንት መቶ) የተዘጋጀውን ሰነድ በመግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳችሁን ግ.ጨ. 02/2018 የመጫረቻ ሰነድ ተብሎ በሕግና በደንቡ መሠረት ታሽጎ መግባት ይኖርበታል። ጨረታው ለ16 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት እለት የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡ ዘግይተው የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አሸናፊው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ላሸነፉባቸው የቴከኖሎጂ ብዜቶች በራሳቸው ወጪ ማዕከሉ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ ፡-
በስልክ ቁጥር፡- 0222250216 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል
