በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለገላን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል አነስተኛ እና ኮድ 3 የሆነ የመጫን አቅሙ 5 /አምስት/ ሰው ያልበለጠ እና በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሰራ አውቶማቲክ የሆነ መኪና ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ገ/ወ/ገ/ፅ/ቤት/ ግ/ጨረታ ቁጥር 002/2018
በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለገላን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል አነስተኛ እና ኮድ 3 የሆነ የመጫን አቅሙ 5 /አምስት/ ሰው ያልበለጠ እና በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሰራ አውቶማቲክ የሆነ መኪና ለ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ15 /ለአስራ አምስት/ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ በገላን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሲንቄ ባንክ ቁጥር 1064793701213 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው/አስራ ስደስተኛው/ የስራ ቀናት በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከረፋዱ እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚውል በባንክ በተረጋገጠ CPO ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት ዋጋ ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ 0913321839/0910742350
በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
