የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ ገልባጭ መኪኖች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የተሽከርካሪው የጉዞ ርቀት |
ዝቅተኛ የስሪት ዘመን |
የመኪና ብዛት |
መለኪያ |
ነጠላ ዋጋ + ነዳጅ + ተ.እ.ታ በብር በ1ሜ.ኪ/ኪ.ሜ |
መለኪያ |
ነጠላ ዋጋ+ነዳጅ+ ተ.እ.ታ ብር በ1ቶን/ኪሜ |
|
1 |
ከ0-5ኪ.ሜ/5 ኪ.ሜ ጨምሮ |
>2013 |
133 |
በ1ሜ.ኪ/ኪ/ሜ |
37.50 |
በ1ቶን/ኪ.ሜ |
37.00 |
|
ከ5-10 ኪ.ሜ/ከ5ኪ.ሜ በላይ 10ኪ.ሜ ጨምሮ |
35.80 |
35.00 |
|||||
|
ከ10ኪ.ሜ በላይ |
34.90 |
33.00 |
አከራይ አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጂናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይየተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መመዝገብ የሚችሉት የተሽከርካሪው ባለቤት ወይም በስማቸው ተሽከርካሪውን ማከራየት እንደሚችሉ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ህጋዊ ውከልና የሚያቀርቡ ብቻ ናቸው።
- አከራይ እንዳመጣጣቸው ቅደመ ተከተል ፍላጎት እስከሚሟላ ድረስ ተመዝግበው በቅደም ተከተሉ መሰረት ለስራው ይጠራሉ፡፡
- ለኪራይ የቀረበው ገልባጭ መኪና የቴክኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት ስለመሆኑ የባለስልጣን መ/ቤቱ የመሳሪያ አቅርቦት አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- የነዳጅ ዋጋ በመንግስት ውሳኔ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የዋጋ ማስተካከያ በውሉ ላይ በሚገለጸው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል፡፡
- አከራዮች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 105 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-15/011-3-71-41-03
አድራሻ፡- ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
