Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Agricultural Cooperatives Federation (የኦሮሚያ የግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ)
  • Address ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ , Phone: 0910645442
  • Websitehttps://www.oromiacooperativefederation.org/
  • Deadline25 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-10-25 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Contractors

የኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር አሰላ ያለው ይዞታ ላይ የግድብ ማስፋፊያና ጥገና በፌዴሬሽኑ በተዘጋጀው ቴከኒካል ስፔሲፊኬሽን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።


2 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን /የተ/የግ/ማኅበር አሰላ ያለው ይዞታ ላይ የግድብ ማስፋፊያና ጥገና በፌዴሬሽኑ በተዘጋጀው ቴከኒካል ስፔሲፊኬሽን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  1. ተጫራቾች General Contractor 5 (GC-5) Water Work Contractor 5 (WWC-5) እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
  2. ተጫራቾች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሌሎች ተያያዥ ሕጋዊ ሰነዶችን አሟልቶ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ ብርበመክፈል የጨረታ ሰነዱን ንፋስ ስልክ ላፍቶ /ከተማ ጀሞ ሚካኤል /ክርስቲያን አጠገብ O.A.C.F ሕንፃ ላይ 6 ፎቅ ኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና /ቤት የቢሮ ቁጥር 12 ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ ለሰነድ ግዥ የሥራ ቀናትን ከሰኞ-አርብ እንድትጠቀሙ እናሳውቃለን።
  4. ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብርቢድ ቦንድ ወይም በሲፒኦ ከፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማቅረብ መጫረት ይችላል።
  5. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት፡-
    1. ጨረታው የሚከፈተው 17ኛው ቀን ሲሆን 17ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ከተገኘበት በዚሁ ዕለት 430 ይከፈታል።
    2. የፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ተደርጎ እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ መቅረብ ኣለበት።
    3. የጨረታው ኮሚቴ በተዘጋጀው የጨረታ መስፈርት መሰረት የቀረበውን የፋይናንሽያል ሰነድ መርምሮ በጨረታው ሰነድ መሰረት የተጫራቾችን ውጤት ያስቀምጣል።
    4. ተጫራቹ ጥሩ የመልካም ስራ አፈፃፀም ሪከርድ ከሌለው፣ የተሳሳተ መረጃና፣ የሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መስጠት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
    5. ፌዴሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
  6. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፌዴሬሽኑ መረዳት ይቻላል።

አድራሻ፡- የኦሮሚያ የግብርና //ማኀበራት ፌዴሬሽን ስልክ ቁጥር፡- 0989 994 491/0910 645 442

 

የኦሮሚያ የግብርና ኀብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን /የተ/የግ/ማኅበር

Save Tender