በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት በጮራ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች የተለያዩ የመኪና አካላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር W/M/A/05
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት በጮራ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ መ/ቤቶች የተለያዩ የመኪና አካላትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ከሚሠሩት (ሚጠገኑት) ተሽከርካሪዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ከሚያቀርቡበት ጠቅላላ ዋጋ 5% ፐርሰንት/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራ አፈጻጸም የጠቅላላ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) ማስያዝ ይኖርበታል
- ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ሲሆን በ23/2/2018 በ4፡00 ሰዓት ላይ አስገብተው በ23/2/2018 በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1079 (አንድ ሺህ ሰባ ዘጠኝ) በቴሌ ብር አካውንት በመክፈል ጮራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በመውሰድ ከጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 /አምስት/ መግዛት ይቻላል።
- ከጠቅላላ ሥራ (ጥገና) ዋጋ 2 ፐርሰንት ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆነ
- ለአሸናፊው ድርጅት ተሽከርካሪዎቹን በድርጅቱ አድራሻ እናቀርባለን።
- አሸናፊው ድርጅት የሚጠግናቸው ተሽከርካሪዎችን ኦሪጂናል ዕቃዎችን የመለወጥ ግዴታ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ ዋጋ በትክክል በመሙላት በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች ኦሪጂናል እና ኮፒውን በማሸግ ማቅረብ አለበት።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኦሪጂናል እና ኮፒ፤ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ኦሪጂናልና ኮፒ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ኦሪጂናል እና ኮፒ ፣የቲን ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኦርጂናል እና ኮፒ እና ሌሎችንም የተለያዩ ደጋፊ ማስረጃዎችን ኦሪጂናል እና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ አለበት።
- ሲፒኦ / CPO/ ለብቻው በታሸገ አንድ ፖስታ መቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ውድድር የሚከናወነው በነጠላ ዋጋ ይሆናል።
- ተሽከርካሪዎችን ለማስገባት የቦታ ርቀት ወሳኝ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ከወረዳችን ከተማ ቢያንስ ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መራቅ የለባቸውም።
- ዋስትና መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤ
የስልክ ቁጥር O47 337 0611/ 047 337 0045/ 09 10 04 99 72
በቡኖ በደሌ ዞን የጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
