በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን ቅ/ጽ/ቤት፤ በስልጢ ወረዳ አሹቴ ቀበሌ እና በምስራቅ ስልጢ ወረዳ ገርቢ በር ላይ፤ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለመጠለያ ግንባታ የሚውሉ ማቴሪያሎች/ዕቃዎችን (የሊሾ አሸዋ፣ ፍልጥ፣ ቋሚ፣ ማገሮች፣ ክፈፍ፣ ውሃ፣ የጤፍ ጭድ፣ አፈር፣ ኮረት ድንጋይ፣ ሞራሌ 8 ቁጥር ሚስማር ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን) የቤቶችን የወለል ስራ ወይም ሊሾ የጉልበት ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግብአትና የጉልበት ዋጋ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን ቅ/ጽ/ቤት፤ በስልጢ ወረዳ አሹቴ ቀበሌ እና በምስራቅ ስልጢ ወረዳ ገርቢ በር ላይ፤ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለመጠለያ ግንባታ የሚውሉ ማቴሪያሎች/ዕቃዎችን (የሊሾ አሸዋ፣ ፍልጥ፣ ቋሚ፣ ማገሮች፣ ክፈፍ፣ ውሃ፣ የጤፍ ጭድ፣ አፈር፣ ኮረት ድንጋይ፣ ሞራሌ 8 ቁጥር ሚስማር ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን) የቤቶችን የወለል ስራ ወይም ሊሾ የጉልበት ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸዉ
- VAT ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ ፤
- ከሀገር ዉስጥ ገቢ አስተዳደር በጨረታዉ ሂደት ጊዜ የሚጸና - በመንግስት ግዢ ስር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ ፤
- የ2017 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- ህጋዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ያለው
- የመልካም አፈጻጻም የምስክር ወይም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ 2 % ማስረከቢያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን እና ህጋዊነቱ ለ90 ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት። ኢንሹራንስ የቼክ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን ቅ/ጽ/ቤት ግዥ፤ ፋይናንስና አስተዳደር ክፍል ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15/2018.0 በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ።
- የጨረታው ሰነድ 1 የዋጋ ማቅረቢያ ፋይናንሻል ... ኦርጂናል (1) እና ኮፒ (1) 2. ቴክኒካል ኦሪጂናል እና ኮፒ (1) በአጠቃላይ የእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች ለብቻቸዉ በሰም በማሸግ የእናት ፖስታ ውስጥ አድርጎ፣ የእናት ፖስታውንም በሰም ማሸግ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከጥቅምት 15 ቀን /2018 ዓ.ም የጨረታ ሰነዱን ማህበሩ ባዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ፣ በዕለቱ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ውስጥ ይከፈታል። ጨረታዉ በተገኙበት በቅርንጫፉ ጽ/ቤት የሚከፈትበተ ቀን በአል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታዉን ሰንድ መግዛት የሚፈልግ በድርጅቱ የስራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ) ከጠዋቱ 2:30 እስከ ከሰዓት 11:30 ከማህበሩ ዞን ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና አስተዳደር ክፍል በአካል በመገኘት የማይመሰስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፍል የጨረታዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወደም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ : ከዚህ በታች ባለዉ ስልክ ቁጥር ዘወትር በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ::
ስልክ: 046-7710008/150 ወይም 0911570744/0913089896/09234060
አድራሻ: በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፤ በማዕከላዊ
ኢትዮጵያ ክልል
የስልጤ ዞን ቅ/ጽ/ቤት /ወራቤ
