የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ሥራ ክፍሎችን የአልምኒየም ፓርቲሽ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ሥራ ክፍሎችን የአልምኒየም ፓርቲሽ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ተፈላጊ ሥራ ለመስራት ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 20,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በተለያዩ ፖስታዎች በመሙላት ፋይናንሽያልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ሥራ አስፈጻሚ ክፍል ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0463299263/0467710368 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
