Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ፡-

  • LOT 1- Workshop Materials - NCB/OACFLTD/AMF/01/2018
  • LOT 2- Electrical Materials - NCB/OACFLTD/AMF/02/2018
  • LOT 3- Electrical and Mechanical tools - NCB/OACFLTD/AMF/03/2018
  • LOT 4- Bearing-NCB/OACFLTD/AMF/04/2018
  • LOT 5- Mechanical Seal and Oil Seal - NCB/OACFLTD/AMF/05/2018
  • LOT 6- Sheet Metals and Angle Iron - NCB/OACFLTD/AMF/06/2018
  • LOT 7- Steam Valves and pipe -NCB/OACFLTD/AMF/07/2018

ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባን 1000043405229 በመፈል /ገቢ በማድረግ/ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ 200-600 ሰዓት፤ ከሰዓት 7:00-1000 ሰዓት ድረስ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል /ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም ሰላቁሉምሳ ከሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 003 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና /ቤት ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከተጠቀሰው የመዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና LOT 1 ብር 15,000.00 LOT 2 ብር 15,000.00 LOT 3 ብር 10,000.00 LOT 4 ብር 10,000.00 LOT 5 ብር 5,000.00 LOT 6 ብር 10,000.00 LOT 7 ብር 10,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለየብቻ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን 22ኛው ቀን LOT 1 እና LOT 2 4:00 ሰዓት ተዘግቶ 430 ሰዓት ላይ፤ LOT 3 እና LOT 4 5:00 ሰዓት ተዘግቶ 530 ሰዓት ላይ፤ LOT 5 LOT 6 እና LOT 7 ልክ 5:40 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 610 ሰዓት ላይ ለመገኘት በሚሹ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የፋብሪካችን ዋና /ቤት የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ ሰባተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። የመፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያና በተጫራቾች መመሪያ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለና ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-65-65-04-81/ 09-65-65-02-85 በሥራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃላ/የተ አሰላ ብቅል ፋብሪካ

 

Save Tender