Tender Detail

Tender Details


በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ጥሬ ዕቃ መለዋወጫዎች እና ሌሎች እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ጥሬ ዕቃ መለዋወጫዎች እና ሌሎች እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

 

የሎት ቁጥር

የእቃው አይነት

ሎት-1

ለተለያዩ የፕላስቲክ ማምረቻ የሚውሉ ግብዓቶች

ሎት-2

የማሽን መለዋወጫዎች ኤሌክትሪካል ፓርቶች

ሎት-3

የማሽን መለዋወጫ መካኒካል ፓርቶች

ሎት-4

የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች

ሎት-5

ለማሽን የሚያስፈልጉ ዘይትና ቅባት

ሎት-6

የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ

ሎት-7

የፅዳት እቃዎች

 

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ - ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
  3. ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርበታል።
  5. ተጫራ የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባን ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት፣ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻችን፡- በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት

 

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ

 

Save Tender