የሚአ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በሮድ ፈንድ በጀት የሚአከ ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው • ሎት 1 ካልቨርት እና ዲች ጥገና ስራ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC ተቋራጮችን • ሎት 2 ካልቨርት እና የጠጠር መንገድ ጥገና ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆነ GCRC/ ለሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚአ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በሮድ ፈንድ በጀት የሚአከ ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው
- ሎት 1 ካልቨርት እና ዲች ጥገና ስራ ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ GC ተቋራጮችን
- ሎት 2 ካልቨርት እና የጠጠር መንገድ ጥገና ለደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ለሆነ
GCRC/ ለሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች
በማሟላት መወዳደር ይችላሉ
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስከ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
3. በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
5. ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ከሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6, የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 1000/አንድ ሺ ብርከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፤
7. የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ሀጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 95,000 ዘጠና አምስት ሺ ብር ለሎት ሁለት 40,000/አርባ ሺ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼከ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ከሬዲት ለሚ አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይሆኖ 16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
10.በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
11.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 1
