የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውልና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች እና የንጽህና/የጽዳት ዕቃዎች ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር፤ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ-03/2018
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውልና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን፤
- ሎት I፤ የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት -II፤ የፕሪንተር ቀለሞች
- ሎት -III፤ የንጽህና/የጽዳት ዕቃዎች
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲሳተፉ መ/ቤቱ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል፤ አዲስ አበባ ከተማ፤ ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፤ 4ኛ ፎቅ፤ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በማየት እያንዳንዱን ዕቃ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Gurantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ጨረታው ሕዳር 01 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለጸው አድራሻ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገለጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በፋክስ በጽሑፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07
ስልክ ቁጥር 011-122-00-20/011-124-02-58
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
