የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2018 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ቀንድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የዳልጋ ከብት ቀንድ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2018 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውን የዳልጋ ከብት ቀንድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል::
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ምርቱ በሳምንት ሁለት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
