ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የእሳት አደጋ መከላከያና ማጥፊያ ስሊንደሮች ሙሌት ግዥ
ሎት 2 የታረደ የሐበሻ ዶሮ አቅርቦት ግዥ
ሎት 3 የአጥንት መቁረጫ /Bon Cutter/
ሎት 4 የድንች መጥበሻ ማሽን /Deep fryer/
ሎት 5 ሰብመርሰብል ወተር ፓምፕ Submersible water pump/
ሎት 6 ቨርቲካል ፓምፕ Vertical Pump/
ሎት 7 ሰርፌስ ፓምፕ Surface Pump/
ሎት 8 የላውንደሪ ማድረቂያ ማሽን Laundry Dryer Machine/
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017/2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገርውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና 2 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ፣ ለሎት 3 እና 4 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) እና ለሎት 5፣ 6፣ 7 እና 8 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመከፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው:
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
8 ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
9 ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
10 ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
11. የጨረታ ሂደቱ የቴከኒከ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 እና 2 ቴክኒካል ሠነድ ግምገማ ናሙና ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) እና ለሎት3፣4፣5፣6፣7 እና 8 የቴከኒክግምገማ ወይም እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ውጤት (55%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (45%) ሲሆን ድምር ውጤት ከioo% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ እና እስፔስፊኬሽን/Specification/ግምገማ ሰነድ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ፣ ናሙናውን ወይም ድርጅታዊ ብቃት እና ቴከኒካል ግምገማ ሠነድ ወይም የግምገማ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ - የመገምገሚያ መስፈርቶቹ
በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/011 5 15 73 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
