በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ት/ት/ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት የእሬሶ አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት ለሴቶች የመጸዳጂያ ክፍል ግንባታና ለመሀል አምባ መዋለ ህጻናት ት/ት ቤት የቦኖ ግንባታ ስራ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/001/2018
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ት/ት/ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት የእሬሶ አንደኛ ደረጃ ት/ት ቤት ለሴቶች የመጸዳጂያ ክፍል ግንባታና ለመሀል አምባ መዋለ ህጻናት ት/ት ቤት የቦኖ ግንባታ ስራ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት/ መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ከተማ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/WWC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) ለሁለቱም ሰነዶች በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ አርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶከመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና መሆን አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
ለበለጠ መረጃ- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር- 0113360162/146 ይደውሉ
በጉራጌ ዞን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
