የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሣምንታዊ የግምጃ ቤት ሰነድን በጨረታ ቁጥር 989 በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ
የጨረታ ማስታወቂያ
- ሣምንታዊ የግምጃ ቤት ሰነድ ጨረታ ቁጥር 989
- ለሽያጭ የቀረበው ሰነድ ጠቅላላ ዋጋ ብር 32,219,615,000
- ሰነዶቹ ለገበያ የሚቀርቡበት ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
- የሰነዶቹ ዓይነትና ለጨረታ የሚቀርበው የገንዘብ ልክ፣
|
የሰነዱ ዓይነት |
የገንዘብ ልክ |
የሚከፈልበት ጊዜ |
|
የ 28 ቀን |
3,221,955,000 |
ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም |
|
የ 91 ቀን |
11,276,890,000 |
ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም |
|
የ 182 ቀን |
12,887,840,000 |
ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም |
|
የ 364 ቀን |
4,832,930,0000 |
ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም |
- የእያንዳንዱ የግምጃ ቤት ሰነድ መነሻ መደብ ብር 5,000 ሆኖ ከዚህ በላይ ለሚፈልጉ የመነሻ ብዜት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለሁሉም ወይም ለየትኛውም የሠነድ ዓይነት መጫረት ይችላል፡፡
- የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ከክፍያና የሂሣብ ማወራረጃ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማመልከቻ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 5፡30 ሰዓት
- የጨረታ ውጤት ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ይገልጻል፡፡
- ከግምጃ ቤት ሰነድ ጋር በተያያዘ የሚገኝ ገቢ ወይም ትርፍ ከማናቸውም ዓይነት ታክስ ነጻ ነው።
- ተጨማሪ መረጃ ከክፍያና የሂሣብ ማወራረጃ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት ወይም ከባንኩ ድረ ገጽ www. nbe.gov.et ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
