Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-681-32-41
  • Website
  • Deadline13 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-11-13 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Electronics Materials , Vehicle tire

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከዚህ በታች የተመለከቱትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥርጨረታ ማስታወቂያ: - 02/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማለትም፡-

1. የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎች፣

2. የጽህፈት መሳሪያዎች፣

3 የውሃ እቃዎች፣

4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣

በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ስለሆነም-

1. የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራቁጥር1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የእቃ ግዥ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6 ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈልበግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

7 የግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤቱ 7.5 ቫትን ይቆርጣል/ይሰበስባል፡፡

8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የውሃ እቃዎች እና ¡ኤሌከትሮኒክስ እቃዎችን ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በመከፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራች የጨረታ ሰነዳቸው በጥንቃቄ አሽገው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

11. የግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ቢሮ ቁጥር22 በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-6-81-32-41 በመወደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

Save Tender