በሲዳማ ብ/ክ/መ/የትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመ/ቤቱ ተሽከርካሪ ጥገና ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018
በሲዳማ ብ/ክ/መ/የትምህርት ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመ/ቤቱ ተሽከርካሪ ጥገና ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 15ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከክልሉ የትራንስፖርት ደረጃ ሶስት የሚገልጽ ብቃት ማርጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- ከላይ የተገለጹ የተሽከርካሪ ጥገና የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ / ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በቴክኒካል ሰነድ ተጫራቾች መመሪያና ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፣
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል።
- በጨረታ ግምገማ ወቅት በሀዋሳ ከተማ ላይ ባሉት ጋርዥ የመስክ ምልከታ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ ቫቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-212-43-07 ደውለው ይጠይቁ።
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ት ትምህርት ቢሮ (ሀዋሳ)
