በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል የቢሮና ላብራቶሪ ሕንፃ የግንባታ ሥራ ለማከናወን ማዕከሉ የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በማቅረብ የባለሙያ የእጅ ዋጋ (Labor cost) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የ የ
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል የቢሮና ላብራቶሪ ሕንፃ የግንባታ ሥራ ለማከናወን ማዕከሉ የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በማቅረብ የባለሙያ የእጅ ዋጋ (Labor cost) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
1. በጨረታው ለመሳተፍ በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ:፡፡
3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያሉ G.C እና B.C የሥራ ተቋራጭ የሆኑ የግንባታ ሥራ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊከ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት የግብር ግዴታቸውን የተወጡና ለ2018 በጀት ዓመት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ማዕከሉ ለማሰራት የፈለገውን የግንባታ ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ)ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተመሰከረ CPO ብቻ በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአዳማ ከተማ ወደ አሰላ ከተማ በሚወስደው መንገድ 17 ኪ.ሜ በሚገኘው መልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ የማይመለስ ብር1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመግዛትና የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ግልፅ ጨረታ ግ.ጨ 03/2018 የመጫረቻ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ተለይቶ በህግና ደንብ መሰረት ታሽጎ መግባት ይኖርበታል ፡፡
ጨረታው ለ20 ተከታታይ ቀናት ከፍት ሆኖ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል ፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ የጨረታው መከፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል ፡፡
ዘግይተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡ -
በስልክ ቁጥር፡-+251222250216 የቢሮ እና 0911942650/0920947151 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲት
