Tender Detail

Tender Details


የቴፒ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የግዥ/ፋ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/ እስቴሽነሪ፣ ሎት 2. ኤሌከትሮኒከስ ላፕቶፕ፣ ዴስከ ቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር፣ ኢብሰን እስካነር፣ CCTV Camera television ሎት 3. ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት የግዥ/ፋ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/ እስቴሽነሪ፣ ሎት 2. ኤሌከትሮኒከስ ላፕቶፕ፣ ዴስከ ቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር፣ ኢብሰን እስካነር፣ CCTV Camera television ሎት 3. ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. የግብር ከፋይነት ምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6 ተጫራቾች ህጋዊ ሰውነት ማቅረብ አለባቸው፡፡

7 ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ በሲፒአ (cpo) በሎት 1 አንድ እስቴሽነሪ 5,000፣ ሎት 2 ዴስክቶፕ ከምፒውተር እና ፕሪንተር፣ እስካነር፣ ላፕቶፕ፣ ቴሌቪዥን፣ ሲሲቲቪ ካሜራ 5,000 ሎት ሶስት ሞተር ሳይክል 5,000 ከታወቀ ባንከ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ቴፒ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ቀርቦ RV የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ cpo የሚያዘጋጀው ድርጅቱ ከሆነ በድርጅቱ ስም በግል/ፕራይቬት ከሆነ ደግሞ በድርጅቱ ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

8 ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 10% ጨረታውን ሲያሸንፉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9 ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን 1/አንድ ኦሪጅናል እና 2 ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በወቅቱ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

10 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሰዓት ቴፒ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን በዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡

11 የድርጅቱ ማህተምና እና ፊርማ በፖስታው ላይ እና ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ እንዲያርፍ ይገደዳል፡፡

12 ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከቴፒ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

13. አሸናፊው ተጫራች ከሎት 1- 3 ያሉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቴፒ ከተማ ፍርድ ቤት በማምጣት በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

 

14 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በደቡብ ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር

የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

Save Tender