ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡-
-
የክራሸር ሮስሮች
-
ልዩ ልዩ ዕቃዎች
-
ልዩ ልዩ ሽቦዎች
-
ስኮርች ኮምፓወንድ
-
ብላደሮች
-
ያገለገሉ መካኒካል ማሽንስና ስፔር
-
ያገለገሉ የኤሌክትሪክ ሞተሮች
-
የጎማ የውስጥ ላስቲኮች ፤ ፍላፖች
በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ።
-
ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው ፡፡
-
የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ ፡፡
-
ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ መሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ጨረታው ህዳር 13 ቀን 2018 ዓም ከጠዋቱ 4:20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
-
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፦- ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ስልከ ቁጥር 011-442-15-55/234 ወይም 0943880372 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማ
