ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚያስገነባቸው ት/ቤቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮችን ከነአክሰሰሪያቸው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚያስገነባቸው ት/ቤቶች ከህጋዊ አቅራቢዎች ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ኮምፒውተሮችን ከነአክሰሰሪያቸው አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋዋል፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፤
- በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የንግድ ምዝገባና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባ /Tin Number/ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ /ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችና የጨረታ ሰነድ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) ገዝተው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ (የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው፡፡ ተጫራች የሚያቀርበው የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላስቀመጠው የእቃው አይነት እና/ ወይንም መስፈርት (Specification) መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው፡፡ ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የንግድ ሰነዶች በሚል ተጽፎባቸው ይቀርባሉ፡፡
- ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በትክክል መሞላት አለበት፤ አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታከስ የማይመለከተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ አይካተትም፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደ ታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው፤ የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ለእያንዳንዱ እቃ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈርም አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ይቆይና በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል። አስረኛው ቀን ቅዳሜ/እሁድ በዓል ላይ ከዋለ የጨረታ መክፈቻው ቀን በቀጣይ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ታይቶ ተቀባይነት ካላገኘ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፤ ይህንን ባያድርግ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠራል፣ የአስያዘው CPO ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት፡፡ ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም፡፡ መ/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም፡፡
- በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በድርጅቱ የግዥ መመሪያ እና በሀገሪቱ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፖስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 2% የመልካም ስራ አፍጻጸም ዋስትና (ውል ማስከበሪያ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም፡፡
- በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- ድርጀቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114 71 42 91 / 0114 71 43 58 በስራ ሰዓት ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት
