በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የስፖርት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት እና የመ/ወ/አስ/ፅ/ቤት G+4 ህንፃ ግንባታ ከደረጃ 1 እስከ 4 GC እና BC በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ማስገንባት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የስፖርት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መግዛት እና የመ/ወ/አስ/ፅ/ቤት G+4 ህንፃ ግንባታ ከደረጃ 1 እስከ 4 GC እና BC በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፤
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሽግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የህንፃ ግንባታውን በተመለከተ የታደሰ የደረጃ ብቃት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የስፖርት እቃዎች በብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን አስከ 15ኛው ቀን እና የህንፃ ግንባታውን በብር 1000 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 20ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስፖርት እቃዎች በቁርጥ 15,000 ብር እና ለግንባታው 0.5% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤታችን የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ውድድሩ የሚካሔደው በግዥ መመሪያው መሰረት ሲሆን መ/ቤቱ ያስቀመጠውን የቴክኒክ መስፈርት ያሟላ ተወዳዳሪ ወደ ፋይናንሽያል ውድድር እንዲያልፍ ይደረጋል፤ ሆኖም የተቀመጠውን የቴክኒክ መስፈርት የማያሟላ ተወዳዳሪ ከጨረታ ውድድር ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የቴክኒክ መስፈርቱ ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ተያይዟል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በእንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እና የቴክኒካል ሰነድ በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ የስፖርት እቃ ማስገባት ይኖርባቸዋል ግንባታውን በተመለከተ በ21ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የስፖርት እቃ ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡01 ሰአት ታሽጐ በ3፡30 ይከፈታል እንዲሁም ግንባታው ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን በ3፡01 ሰአት ታሽጐ በ3፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-13-20-136/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የመርሐቤቴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
