Tender Detail

Tender Details

  • Company ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 (ባህር ዳርዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) እና አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-0538
  • Websitehttps:// zcc.org.et
  • Deadline21 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-21 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Aluminium Supply and Work

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባው ለባህርዳር ገቢዎች ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ለአልሙኒየም እና አክሰሰሪወች ግብአቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለሚገነባው ለባህርዳር ገቢዎች ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ለስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ለአልሙኒየም እና አክሰሰሪወች ግብአቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ ጋብዞ እና አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ዘመን

ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የባህር ዳር የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማእከል ለባህርዳር ገቢዎች ፕሮጀክት ግንባታ ለአልሙኒየም ስራ የሚያስፈልጉ አልሙኒየም እና አክሰሰሪ አቅራቢዎችን በመጋበዝ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

      1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ
      2. ሁሉም ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
    1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ 200(ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
    3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 200 እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ድረስ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
    4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ ብቻ ቅርንጫፋቸው ባህርዳር ከተማ ከሚገኙ ባንኮች ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
    5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ከቀኑ 830 ሰዓት ይከፈታል።
    6.  የጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገፅ እና ፖስታ ላይ የተጫራቾ ፊርማ እና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
    7. ተጫራቾች ከስፔክ ውጭ ዋጋ የሚሞሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
    8.  ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከአሸናፊው ድርጅት ላይ ከገዛው እቃ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
    9.  የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
    10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በባህርዳር ለማምረቻ ማምረቻ ማእከል ለሚገኘው ንብረት ክፍል ማስረከብ አለበት። ናሙና የሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ቀድመው ናሙና አቅርበው ሲጸድቅላቸ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸትል።
    11. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
    12. አሸናፊው ድርጅት እቃውን ባያቀርብ ያስያዘው ሲፒኦ ተወርሶ ወደ መስሪያ ቤቱ አካውንት ገቢ ሆኖ ሁለተኛ አሸናፊው በአንደኛው አሸናፊ ዋጋ እንዲያቀርብ ፍቃደኛ ከሆኑ ውለታ ይዘው ሊጋበዝ ይችላል።
    13. ማንኛውም አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች እርከከብ የሚያደርገው ማምረቻ ማእከሉ ነበረት ክፍል ይሆናል። ስለሆነም አሸናፋው ድርጅት ከፍያ የሚጠይቀው ሙሉ እቃውን ለድርጅቱ ንብረት ክፍል ገቢ አድርጎ የገቢ ደረሰኝ ያቀርብ የሚከፈል ይሆናል።
    14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
    15. አሸናፊው ድርጅት ውለታ ሲይዝ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒአ ብቻ ቅርንጫፋቸው በባህርዳር ከተማ በሚገኙ ባንኮች ማስያዝ አለባቸው፡ አሸናፊው ድርጅት ውለታ ይዞ እቃውን ባያቀርብ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ተወርሶ ወደ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
    16.  በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 33 99 78 62 /058 320 1019 ይችላል።

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የባህርዳር የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማእከል ባህርዳር

Save Tender