በጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮግራም በእንደጋኝ ወረዳ በበቻ ት/ቤት የወንዶች መጸዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮግራም በእንደጋኝ ወረዳ በበቻ ት/ቤት የወንዶች መጸዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በዚሁ በግልጽ ጨረታ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
መስፈርት
- ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት /VAT/ ተመዝጋቢ እና ህጋዊ ማስረጃቸውንና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ ከእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዢና/ን/አስተዳደር ስ/ሂደት 500 /አምስት መቶ ብር/ ከገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የንግድ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 20,000 /ሀያ ሺ/ ብር በእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በአን ላየን የተመዘገበ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ በሚነበብ የእጅ ፅሁፍ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ፤ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በላዩ ላይ ኮፒ እና ኦሪጅናል መሆኑን በመፃፍ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በመጨመር /በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት /15/ ከቆየ በኋላ በአስራ አምስተኛው ቀን ግዢና/ን/አስተዳደር ስ/ሂደት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
ስልክ ቁጥር 011-35-00-47/46
በጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
