የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት በሚያካሂዳቸው የሀገር ውስጥ ውድድሮች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ደረጃውን የጠበቀ የሜዳሊያ፣ የዋንጫ እና ሪቫን ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2018 በጀት ዓመት በሚያካሂዳቸው የሀገር ውስጥ ውድድሮች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸውን ደረጃውን የጠበቀ የሜዳሊያ፣ የዋንጫ እና ሪቫን ግዥ በሀገር ውስጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መስብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ እና ላምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱት በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
አድራሻ:- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ:- 0116-47-97-94/0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ፋክስ 0116-45-08-79 ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
