ፀደይ ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ሁለት ሚድ ባሶች እና አንድ ቮልስ ዋገን አዉቶሞቲቭ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/001/2018
ፀደይ ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ሁለት ሚድ ባሶች እና አንድ ቮልስ ዋገን አዉቶሞቲቭ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው አይነት |
ብዛት |
ሞዴል |
የምርት ዘመን |
የመጫን አቅም |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
መኪኖቹ የሚገኙበት ቦታ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ |
|
1. |
አነስተኛ አውቶብስ |
2 |
Daewoo |
2013 GC |
22 ሰው |
5,000,000.00 |
ባህርዳር |
አዲስ አበባ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት |
|
2. |
አውቶሞቢል |
1 |
Volkswagen SURAN |
2008 GC |
4 ሰው |
1,100,000.00 |
አዲስ አበባ |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ግለሰብ /ድርጅት/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
- በጨረታው በሁሉም አይነት ወይም በከፊል መወዳደር ይቻላል
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የመኪና አይነቶች የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው የዋጋ ፎርማት ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል። ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል። ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ከበዛበትና ግልፀኝነት ከጐደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሰረዛል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2 % በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ 90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሁለት መቶ ብር /200.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ህዳር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረም።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0918765547/0918713421
ፀደይ ባንክ አ.ማ
