በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች የሚያቀርቡለትና የሚሰሩለት ድርጅቶች ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ለ2018ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1) ደንብ ልብስ
- ሎት 2) የሰራተኞች ደንብ ልብስ ተሰፍቶ የተዘጋጀ
- ሎት 3) የፎቶ ኮፒ እና የፕሪንተር ቀለም
- ሎት 4) የአይሲቲ ዕቃዎች
- ሎት 5) የዕዳት ዕቃዎች
- ሎት 6) ቋሚ ዕቃ
- ሎት 7) የስልጠና አገልግሎትና ምርምር ስራዎች
- ሎት 8) የጉድጓድ ውሃ for demobilization,well rehabilitation and pump reninstallation የጥገና ስራ
- ሎት 9) የላውንደሪ ማሽን
- ሎት 10) የላውንደሪ ማሽን ጥገና
የሚያቀርቡለትና የሚሰሩከት ድርጅቶች ይፈልጋል። በመሆኑም፦
ከላይ ለተጠቀሰው የሚቀርቡ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ከሚያቀርቡት እቃ ጋር የተዛመደ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/፤ የVAT ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚገለፅ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ሰነዱን ሆስፒታሉ ግቢ በሚገኘው የመንግስት ሂሳብ እና ከፍያ ደጋፊ የስራ ሂደት በመምጣት መግዛትይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ
- ሎትı)ለደንብ ልብስ ብር40,000.00(አርባ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፤ በሲፒአና የባንክ ዋስትና
- ሎት 2) ለሰራተኞች ደንብ ልብስ ተሰፍቶ የተዘጋጀ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ
- ሎት 3) ለፎቶ ኮፒ እና የፕሪንተር ቀለም ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና
- ሎት 4) ለአይሲቲ ዕቃዎች ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦናየባንከ ዋስትና
- ሎት 5) ለፅዳት ዕቃዎች ብር 40,000.00(አርባ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና
- ሎት 6) ለቋሚ ዕቃ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ) በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንከ ዋስትና
- ሎት 7) ለስልጠና አገልግሎትና ምርምር ስራዎች ብር 10,000.00(አስር ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንክ ዋስትና
- ሎት8) ለጉድጓድ ዉሃ for demobilization,well rehabilitation and pump reninstallation የጥገና ስራ ብር 500,000.00(ሃምሳ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንከ ዋስትና
- ሎት 9) ለላውንደሪ ማሽን ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ )በጥሬ ገንዘብ በሲፒኦና የባንከ ዋስትና
- ሎት 10) ለላውንደሪ ማሽን ጥገና ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ)በጥሬ ገንዘብ፡በሲፒኦ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመግለጽ አንድ ኦሪጅናል ፋይናንሻል ፤ አንድ ኦሪጅናል ቴከኒካል አንድ ኮፒ ፋይናንሻል፤ አንድ ኮፒ ቴከኒካል በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው ሆስፒታሉ ባዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቹ ወደ ጨረታዉ ሳጥን ፖስታውን ሲያስገባ ቴከኒካል ለብቻ ፋይናንሻል ለብቻ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እና ተጫራቹ ፋይናንሻሉ እና ቴክኒካሉን በአንድ ፖስታ ካስገባ ጨረታዉ ወዲያውኑ ወድቅ ይሆንበታል።
4. ጨረታው በሚያበቃበት የመጨረሻ ቀን(በአስራ አንደኛዉ ቀን)ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ በ4:30 በሆስፒታሉ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. የበለጠ ማስረጃ ቢያስፈልግዎት በስልከ ቁጥር 0115-25 68 23 ደውለው ይጠይቁ።
6. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል
