የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር WESSF /LP/013/2025
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ምድብ/Lot |
Description |
|
1 |
Motor Cycle 150cc-185cc |
|
2 |
በቆሎ፣ ፉርሽካ፣ ጥፍጥሬ፣የኑግ ፋጉሎ፣ የምስር ገለባ፣ የባቄላ ገለባ እና ጨው |
|
3 |
Circular Hollow steel, flat Iron & Rebar |
|
4 |
Mettler Toledo and Cold water Bath (JULABO) |
|
5 |
Supply & Installation of Uninterrupted power supply (UPS) |
|
6 |
የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ኪራይ ባለ 32 ወንበር |
|
7 |
የፍሳሽ ቆሻሻ ማንሻ መኪና ኪራይ (Ceaspool car) የመጫን አቅም 10,000-15,000 Lit |
- በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለእያንዳንዱ ምድብ ለየብቻ የማይመለስ 400 / አራት መቶ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000473232708 በጨረታ ተሳታፊው ድርጅት ስም ገቢ በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት ግዥዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ ።
ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 አዲስ አበባ
ለተጨማሪ መረጃ 0115585229/0984550101/0968482445
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር ለጨረታ ማስከበረያ የሚውል ለሚያቀርቡት የጠቅላላውን 2% (ሁለት ፐርሰንት) የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሠነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በየምድቡ ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 ተከታታይ ቀናት 6፡00 ሰዓት ከመሆኑ በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 201 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ። ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚሆን ሲሆን ትክክለኛ የሥራ ቀን በጨረታ ሠነዱ ውስጥ ይጠቀሳል።
- ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወንጂ/ሸዋ ስኳር ፋብሪካ
