ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጨረታ ቁጥር 2/2018 ዓ.ም ለስልጠና እና ለገፀ ምድር ማልማትና ማስዋብ ስራ ግዥ ለመፈጸም 2ኛ ዙር የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጨረታ ቁጥር 2/2018 ዓ.ም ለስልጠና እና ለገፀ ምድር ማልማትና ማስዋብ ስራ ግዥ ለመፈጸም 2ኛ ዙር የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ስለሚፈልግ፦ ሎት
- የገፀ ምድር ማልማትና ማስዋብ ስራዎች
- የስልጠና ማሽነሪ ጥገና ስራዎች
- የኮንስትራክሽን ስልጠና እቃዎች
- የከተማ ግብርና እቃዎች እና የእንስሳት መኖዎች
ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የጨረታው መስፈርቶች፡-
- ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር (Vat) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የ Tin No ሰርተፍኬት እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ለጨረታ የሚሆን ክሊራንስ ያለው
- የተሰማራበት ስራ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የደረጃ እድገት ያላቸው
- ደረጃ ሰባት ሆኖ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ስራ ዘርፍ የሆነና የገፀ ምድር ማስዋብ ስራ ላይ የተሰማራ
- ኢንተርፕራይዝ ከሆነ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት LMIS ሙሉ መረጃቸው የተመዘገበ መሆን አለባቸው።
- ስድስት ወር ያልሞላው ከስራው ጋር ተዛማጅነት የሆነ መልካም የስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ከመንግስት ተቋም ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያገናዘበ ስራ ዝርዝር ማለትም ከገበያ ዋጋ የተጋነነ ነጠላ ዋጋ (unit rate) በከፍታ ወይም በዝቅታ ተሞልቶ ካገኘ የስራው ተቋራጮች (cost break down) ሰርተው እንዲያቀርቡ ያስገድዳል።
- ተጫራቾች በስራው ዝርዝር በሙሉ ሆነ በአንዳንድ ተራ ቁጥር ላይ ዋጋ አለመሙላቱ (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በራሱ ወጪ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የገፀምድሩን ሳይት ማየት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የግዥ ዓይነት (ሎቶች) ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም የፕሮጀክት ዋጋ 2% ማቅረብ የሚችሉና የዋስትና ደብዳቤ ከተደራጀበት ወረዳ ማቅረብ የሚችል። በባንክ ጋራንቲ እና የዋስትና ደብደቤ በNifas Silk poly Technic Collage (ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ) በሚል በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሳተፉ
- ማሽነሪ ማቴሪያል እስኬጁል ማቅረብ የሚችል
- ስራውን ለመስራትና በተሰጠው ጊዜው ለማጠናቀቅ ቃለ መኋላ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መውሰድ ይችላል።
- ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ቴክኒካል ኦርጅናል በአንድ ፖስታ፣ ኮፒውን ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በአንድ ፖስታ በማድረግ በጠቅላላ በ2 በታሽገ ፖስታ በማድረግ ለመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 101 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም እና ፊርማ አድርጎ የማያቀርብ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም። ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድር ወጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለጨረታ በሚመጡበት ጊዜ ህጋዊ ሰነድ ይዞ ማቅረብ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያና ህጋዊ ውክልና ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተራ ቁጥር 6፣7፣9፣10፣11፣12፣13፣14፣15፣16 ላይ የተጠቀሰው መስፈርት ለገፀ ምድር ማልማት እና ማስዋብ ስራ ተጫራቾች ሲሆን ከተጠቀሱት ተራ ቁጥር ውጪ ያሉት ለሁሉም ሎቶች ግዴታ ሆኖ ያገለግላል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጎተራ ኦይል ሊቢያ ዴፖ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0114-70-70-78
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
