የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ማሸነሪዎች (ዶዘር፣ እስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ዳምፕ ትራክ፣ ሻዋር ትራክ፣ ሎቤድ) እና የተለያዩ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 012/2018
የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ ማሸነሪዎች (ዶዘር፣ እስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ዳምፕ ትራክ፣ ሻዋር ትራክ፣ ሎቤድ) እና የተለያዩ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀውን የተጫራቶች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
የጨረታ ዝርዝር ሁኔታዎች
የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከመልከ ኖኖ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሣብ ቁጥር 1054472341218 ገቢ በማድረግ ዲፖሲት ሲልፑን/ Deposit slip መልከ ኖኖ ክ/ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በፌዴራል ገ/ሚኒስቴርወይም ኦሮሚያ ዝቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO (ሲፒኦ) 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ለማሸነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፍ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ነዳጅን፣ የመኪና ቅባት፣ ጥገናውንና የሹፌርና ረዳት አበል እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በተጫራቹ ድርጅት (አከራይ) የሚሸፈን ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ማሽነሪዎችን በራሳችሁ ወጪ መልከ ኖኖ ክ/ከተማ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የልማት ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚያቀርቡት ማሽነሪ ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ህጋዊ የኪራይ ውል አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ።
- አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት መልከ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መልከ ኖኖ ከ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
