የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በ2018 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር - አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ 0002/2018 ዓ.ም ለአካዳሚው ስልጠናና የተለያዩ የውይይት መድረኮች የሚሰጡ የመስተንግዶ አገልግሎቱን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በ2018 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር - አ/አ/አ/አካ/ግ/ጨ 0002/2018 ዓ.ም ለአካዳሚው ስልጠናና የተለያዩ የውይይት መድረኮች የሚሰጡ የመስተንግዶ አገልግሎቱን በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ተጋብዟል፡-
- የንግድ ስራ ፈቃድ የምስክር ወረቀት
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN)
- የአቅራቢነታቸውን ሁኔታ የሚገልፅ ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የተእታ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT)
- ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ
- የጨረታ ሂደቱ የመንግስትን የጨረታና የግዥ ሂደት የተከተለና በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ ከብረሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ወደ ፒያሳ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ላይ በሚገኘው ዳብር ህንፃ ሦስተኛ ፎቅ የግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ በብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) የብር መጠን ያለው የጨረታ ማስከበሪያ "ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ” በሚል አድራሻ በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ወይም ቅድመ ሁኔታ ባላስቀመጠ የባንክ ዋስትና ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በሚል አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሁለት (2) ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ተጫራቾች አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ የቴክኒካል ሰነዶችን እና የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O)፣ በማለት በኦርጅናል እና በኮፒ እንዲሁም ዋጋ የያዘውን ፋይናንሻል ሰነድ በአርጅናል እና ኮፒ በማዘጋጀት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከአካዳሚው በወሰዱት የጨረታ ሰነድ የተጠየቁትን ሞልተውና እያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በመምታት መመለስ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ አስራ አንደኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ በሚገኘው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አካዳሚው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ካስፈለገ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ስልክ ቁጥር 0116-67-33-90 ደውለው ይጠይቁ።
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ
