አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገሉ YTO-130 የሆነ የእርሻ ትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ጨረታ ማስታወቂያ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገሉ YTO-130 የሆነ የእርሻ ትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 በመክፈል የጨራታ ሰነዱን ከአርባጉጉ የገ/ሕ/ስራዩኒየን ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑንና ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ወይም መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቹ ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል የሆነ የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታውን 10% በ CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
- ተሸከርካሪዎችን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ጊቢ ውስጥ ሙግር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ማየት ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአርባጉጉ የህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ተዘግቶ በ5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ጨረታው በ 16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት በ5፡00 (ሰዓት) ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።
- ተጭራቾቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ትራክተሮቹን መውሰድ አለባቸው።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በመገኘት ወይም
በስ.ቁ. 09 21 09 68 80 / 09 20 06 31 65 / 09 17 03 43 43 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
አድራሻችን፡- አርባጉጉ የገ/ሕ/ሥራ/ ዩኒየን አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ
አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ
