የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ የዶሮ እና የንብ እርባታ ሼድ ግንባታ ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሼድ ግንባታ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 122/18
የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ የዶሮ እና የንብ እርባታ ሼድ ግንባታ ግዥ አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የሥራው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
የዶሮ እና የንብ እርባታ ሼድ በዲላ ዙሪያ ወረዳ ዲላ ከተማ |
ሎት 1 |
2 |
|
2 |
የዶሮ እና የንብ እርባታ ሼድ በአረ ዞን ጅንካ ከተማ |
ሎት 2 |
2 |
|
3 |
የዶሮ እና የንብ እርባታ ሼድ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ |
ሎት 3 |
2 |
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት ምዝገባ፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀን የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋቸው 2% ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለጨረታው የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ በ30ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በዲላ ከተማ ከሚገኘው ግብርና ቢሮ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461310134
ማሳሰቢያ፡ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ሎት ብቻ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
