በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት1. በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ጎማ ሎት2. ለካሜራ አገልግሎት የሚውል ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት1. በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች፣ ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ጎማ ሎት2. ለካሜራ አገልግሎት የሚውል ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የታደሰ የዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውንመስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ተጫራቾች ስጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ
- ለሎት 1. ለተሽከርካሪ ጎማ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- ለሎት 2 ለካሜራ ዕቃዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፡፡
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ ጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኋላ ለ3 ወር ማለትም ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0461310108 መደወል ይችላሉ፡፡
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት
