በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለተለያዩ ወረዳዎች የግንባታ ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/06/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለገ/ጉ/ወ ወረዳ ውሀና ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ለሚያሰራው የአመቶ ቀበሌ ሆርሆሮ ምንጭ ግንባታ የአመቶ ቀበሌ ወንዝ ምንጭ ጥገና ጠይባ ቀበሌ ቁለታ ምንጭ መልሶ ግንባታ ከነ ማስፋፊያ ጠይባ ቀበሌ አመዴ ምንጭ ግንባታ አስፈዲን ቀበሌ ጉዋን ምንጭ ግንባታ መጎራጉር ቀበሌ አምበር ወንዝ መልሶ ግንባታ ጊጨዲምቱ ቀበሌ ደመላሽ ምንጭ - ግንባታ የጊፊጩ ዲምቱ ቀበሌ ምንጭ ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/GC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች የቫት 75% ተቀናሽ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጅቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረሰ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው። ውል የሚጸናው ለ90 ቀናት መሆኑን እገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ21ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ተጫርተው ከሻነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ ውል የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- ተወዳዳሪዎች የቫት በመደበኛ በጀት በውሀ ዘርፍ ከዚያ በላይ ፕሮጀክት የያዘው መወዳደር አይችልም።
- ተበዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅድመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን።
ለበለጠ መረጃ፡-የ/ጉ/ከ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360631/146 ይደውሉ
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
