በአብክመ የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎትı ለማህበረሰብ ት/ቤት የአጥርሥራ ሎት2 ለጎንደር ትም/መለ/ከ/ስርጭት የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሎትı ለማህበረሰብ ት/ቤት የአጥርሥራ ሎት2 ለጎንደር ትም/መለ/ከ/ስርጭት የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሚመለከተው የንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / ያላቸው ::
3. የግዥው የብር መጠን 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለበት ለዚህም ማረጋገጫ የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎትı ለተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡ ሎት2 ለተከታታይ 15 ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡ ሎትı በ22ኛው ቀን 3:35 ታሽጎ በ4፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡ሎት2 በ16ኛው ቀን 3፡35 ታሽጎ በ4፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡ነገር ግን ቀኑ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠ/ዋጋ 1.5% በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማርኛ የተተረጎመ የባንከ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጎ/መ/ት/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር G1 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጎንደር/መም/ትምህርት ኮሴጅ
