Tender Detail

Tender Details


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ II በጀት የአብክመ ትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ II የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  


ልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር -06 /2018.

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ II በጀት የአብክመ ትምህርት ቢሮ የአህዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ዋሽ II የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል 

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1.     በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3.     የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው

4.     ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀናት ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

6.     የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመፈል ከገንዘብ ያዥ ፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ የኤሌትሮኒ ዕቃዎች /ላፕቶፕ ኮምፒውተር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ኤክስተርናል ሀርድ 10,000.00 /አስር ሺህ/ ዲጅታል ካሜራ 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ ኤልስዲ ፕሮጀተር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ እና ፍላሽ ባለ 64 ጂቪ 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮ ህጋዊ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለበት

8.     የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና 16ኛው ቀን 400 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡

9.     ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 16 ኛው ቀን 400 ታሽጎ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ስትመጡ በቢሮው አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባን ቁጥር 1000012857253 ወይም አባይ ባንከ ቁጥር 2012116113625016 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ የምትወስዱ ይሆናል፡፡

12. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬቶሬት ፍል በግንባር በመቅረብ በፋ ቁጥር 058 222 0814 በመላ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 62 67/0583203999 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender