አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር, አአከአአድ/ብግጨቁ/021/2018 የሴኪሪቲ ካሜራዎች (ሎት 1) ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የቢሮ ፈርኒቸር (ሎት 3) እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች (ለህንጻ ጥገና) (ሎት 4) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር, አአከአአድ/ብግጨቁ/021/2018 የሴኪሪቲ ካሜራዎች (ሎት 1) ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የቢሮ ፈርኒቸር (ሎት 3) እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች (ለህንጻ ጥገና) (ሎት 4) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
- በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)
- በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
- የታከስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ለሎት 1 (የሴኪሪቲ ካሜራዎች) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ)፣ ለሎት 2 (የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ)፣ ለሎት 3 (የቢሮ ፈርኒቸር) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) እና ለሎት 4 (የኮንስትራክሽን ዕቃዎች - ለህንጻ ጥገና) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።
በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፤
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 0118 21 22 14
የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
