Tender Detail

Tender Details


አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/018/2018 የጽህፈት መሳሪያዎች (ሎት 1)፣ የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 2)፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች (ሎት 3)፣ የመስተንግዶ ዕቃዎች (ሎት 4) እና የተሽከርካሪ ንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች (ሎት 5) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር ከአአድ/ብግጨቁ/018/2018 የጽህፈት መሳሪያዎች (ሎት 1) የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 2) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች (ሎት 3) የመስተንግዶ ዕቃዎች (ሎት 4) እና የተሽከርካሪ ንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች (ሎት 5) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)!
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAI Certificate)
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባን ጋራንቲ ለሎት 1 (የጽህፈት መሳሪያዎች) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ለሎት 2 (የጽዳት ዕቃዎች) ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ) ለሎት 3 (የኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) ለሎት 4 (የመስተንግዶ ዕቃዎች) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) እና ለሎት 5 (የተሽከርካሪ ንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (600 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመከፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው /ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶከመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 . ጠዋት 400 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡

ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2018 . ጠዋት 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ስልክ ቁጥር፡ 0118 21 22 14

 

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender